Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 1 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

 

ምክር ቤቱ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ-ጉባዔ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

 

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

 

ጉባኤው በአዲስ አበባ ከተማ ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የኦዲት ዘገባ ቀርቦ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅም ተገልጿል።

 

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይም ውይይት በማድረግ ያጸድቃልም ተብሎ ነውቅ የሚጠበቀው።

 

በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 ረቂቅ የበጀት አዋጅ ተወያይቶ በማጽደቅና ልዩ ልዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ጉባኤውን ያጠናቅቃል ተብሎ ያጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.