Fana: At a Speed of Life!

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሐ ግብርን አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ዓመታዊ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት መርሐ ግብርን አስጀምረዋል።

 

በመርሐ ግብሩ ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)፣ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር  ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፥ ”የመረዳዳት ባሕላችን የአንድነታችንና የአብሮነታችን ማጠናከሪያ ነው” ብለዋል።

 

በክልሉ ዓመታዊውን የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት መርሐ ግብር  በዛሬው ዕለት ማስጀመራቸውንም ገልጸዋል።

 

ዜጎች ያላቸውን እውቀት እና ጉልበት አስተባብረው በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን ለመደገፍ በሚደረገው ርብርብ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.