Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ እና ሐረሪ ክልሎች የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ እና ሐረሪ ክልሎች የትምህርት ቤቶች መሠረተ ልማት ማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ ተጀምሯል፡፡

በደቡብ ክልል ሕዝባዊ ንቅናቄውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን የቡኢ አዳሪ ት/ ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ አስጀምረዋል፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷በሀገሪቱ ሁሉም ዜጋ በፍትሃዊነት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የሀገሪቱ የወደፊት ትውልድ መሪዎች ከሁሉም ክልሎች በችሎታቸውና በብቃታቸው ተመርጠው የሚማሩባቸው 50 አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡም ገልጸዋል።

ከነዚህ ትምህርት ቤቶች መካከልም አራቱ ግንባታቸው በዚህ ዓመት እንደሚጀመር ነው የተገለጸው፡፡

በጉራጌ ዞን በቡኢ ከተማ የሚገነባው የቡኢ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት አንዱ መሆኑን የትምህር ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በሐረሪ ክልል ትምህርት ለትውልድ ክልል አቀፍ የትምህርት ቤቶች መሰረተ ልማት የማሻሻል ሕዝባዊ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ንቀናቄውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ እና የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) አስጀምረዋል፡፡

ወ/ሮ ሚስራ አብደላ ÷ከደረጃ በታች የሚገኙ ትምህር ቤቶችን በማሻሻል ረገድ ሁሉም አሻራውን በማኖር የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.