Fana: At a Speed of Life!

ቅዱስ ጊዮርጊስና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 30ኛ ሳምንት እና የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስን ያገናኘው የሊጉ የመጨረሻ ጨዋት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማን ግብ አጥቂው ቢኒያም ጌታቸው ሲያስቆጥር÷ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ ያደረገችውን ግብ ደግሞ በረከት ወልዴ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ64 ነጥብ በአንደኝነት ሲጨርስ÷ ድሬዳዋ ከተማ በ40 ነጥብ 10ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ በ25 ግቦች የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የውድድር ዓመቱን አጠናቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.