Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገልን መልካም አቀባበል ከችግርና ሞት ታድጎናል – ሱዳናውያን ስደተኞች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግሥት ድንበሩን ክፍቶ አድርጎ ባደረገልን መልካም አቀባበል ከችግርና ከሞት ታድጎናል ሲሉ በሱዳን ግጭት ተሰደው በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የተጠለሉ ሱዳናውያን ስደተኞች ገለጹ።

ስደተኞቹ እንደገለጹት÷በኢትዮጵያ የተደረገላቸው አቀባበል እና ድጋፍ በስደት ወቅት ሊደርስባቸው ከሚችል እንግልትና ስቃይ ታድጓቸዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ ወጣት አብዱልከሪም ሙሃመድ እንዳለው÷በሱዳን በተከሰተ ግጭት ምክንያት ከአገሩ ተሰዶ ላለፉት ሦስት ወራት በመተማ ዮሐንስ መጠለያ ጣቢያ እያሳለፈ ይገኛል።

እሱን ጨምሮ በርካታ ስደተኞች ወደ መተማ ሲገቡ በኢትዮጵያ መንግስት መልካም አቀባበልና ድጋፍ እንደተደረገላቸው ጠቅሶ÷ለእዚህም ያለውን ምስጋና ገልጿል።

ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ቀን ጀምሮ ምግብ፣ የመጠጥ ውሃና መጠለያ እያገኙ መሆናቸውን ጠቅሶ÷ አንዳንዴ የሚስተዋለው የምግብና መድሐኒት እጥረት እንዲስተካከል ጠይቋል።

ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ትልቅ አክብሮትና ምስጋና አለኝ” ያሉት ደግሞ ሌላኛዋ ሱዳናዊ ተፈናቃይ አሚራ ሙሃመድ ናቸው።

በሱዳን በተፈጠረ ግጭት ከ13 የቤተሰብ አባላት ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደመጡ ገልጸው÷ወደ ኢትዮጵያ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በፍቅር እንደተቀበሏቸው ተናግረዋል።

በመጠለያው በቆዩባቸው ጊዜያት የምግብና የውሃ ድጋፍ እያገኙ ቢሆንም ለሕጻናት ልዩ እንክብካቤ በማድረግ በኩል የተወሰኑ ክፍተቶች አሉም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አቶ አብዱላዚዝ ሀሰን በበኩላቸው÷የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ያደረጉልን አቀባበል የባዕድነት ስሜት እንዳይሰማን አድርጓል ብለዋል።

በመተማ መጠለያ ጣቢያ ምግብ፣ ውሃና ማረፊያ ከማቅረብ ጀምሮ የጤና ምርመራ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.