Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በእሳት አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ በአንድ ሆቴል ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፥ አደጋው ትናንት ምሽት 3:30 ላይ ነው የተከሰተው።

በአደጋውም÷ በሆቴሉ አልጋ ይዘው ተኝተው የነበሩ ዕድሜያቸው 26 እና 24 የተገመተ ወንድና ሴት ወጣቶች በጭስ ታፍነው ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል።

ሟቾቹ ወደክ ፍለሀገር የሚሄዱ መንገደኞች እንደነበሩም አስታውሰዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አምስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ዐርባ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በማሰማራት እሳቱ ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር ችሏል ነው ያሉት።

የእሳት አደጋውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠርም 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ መፍጀቱን ነው አቶ ንጋቱ ያረጋገጡት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.