Fana: At a Speed of Life!

200 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ በካናሪ ደሴቶች መጥፋቷ ተሰማ  

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 200 ሰዎችን አሳፍራ ወደ ስፔን ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ ፍለጋ እንደቀጠለ መሆኑን የስፔን የነፍስ አድን ሰራተኞች አስታወቁ።

ከደቡባዊ ሴኔጋል ተነስታ ወደ ካናሪ ደሴት እያመራች ነበር የተባለችው የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ህጻናትን ጨምሮ 200 ፍልሰተኞችን አሳፍራ እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።

ጀልባዋ ከስፔኗ ቴኔሪፌ 1 ሺህ 700 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው እና ካፎንቴን ከተባለችው  የሴኔጋል የባህር ዳርቻ ከተማ መነሳቷን ዘገባው አመላክቷል።

በጀልባዋ ላይ በርካታ ህፃናት ተሳፍረው እንደነበር ያስታወቀው የነፍስ አድን ቡድኑ፥ ቀደም ሲል በርካታ ሰዎችን የጫኑ ሁለት ጀልባዎች በዛው አካባቢ መጥፋታቸውን አስታውሷል፡፡

ጀልባዋን ለመፈለግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ከነፍስ አድን ሰራተኞች በተጨማሪ በአውሮፕላን የታገዘ ፍለጋ እየተደረገ መሆኑን የስፔን ባህር ሀይል አስታውቋል፡፡

ጀልባዋ በፈረንጆቹ ሰኔ 27 ቀን ከሴኔጋል መነሳቷን የስፔኑን ኢፌ ኒውስ ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.