Fana: At a Speed of Life!

በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ የውጭ ሀገር ገንዘብ እና አደገኛ ዕፅ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ የውጭ ሀገር ገንዘብና አደገኛ ዕጽ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገለፀ።

በዚህም መነሻውን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አድርጎ በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ዱባይ ይወጣ የነበረ 44 ሺህ 440 ዩሮ፣ 11ሺህ 850 የአሜሪካ ዶላር፣ 20 ሺህ 480 ፓውንድ፣ 3ሺህ 700 ድርሃም፣ 300 የሲዊዝ ፍራንክ እና 1ሺህ 700 የሳውዲ ሪያል ከነተጠርጣሪዎች መያዙ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መነሻውን ብራዚል ሳኦፖሎ አድርጎ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ሌሎች ሀገሮች ሊተላለፍ የነበረ በዱቄት መልክ የተዘጋጀ 17 ነጥብ 90 ኪሎ ግራም ኮኬይን አደገኛ ዕፅ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ፍተሻ ከሦስት የውጭ ሀገር ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙ ታውቋል።

መሰል የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ የፀጥታ አካላቱ እየወሰዱት ያለው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መገለፁን ከፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.