Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ “ምርጥ የጉምሩክ ኮሚሽነር” ሽልማትን አገኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ “ምርጥ የጉምሩክ ኮሚሽነር” ሽልማትን አግኝተዋል።

መቀመጫውን ለንደን ያደረገው “አፍሪካ ሊደርሺፕ መጋዚን” የተሰኘ የሚዲያ ኩባንያ ያዘጋጀው ስምንተኛ ዓመታዊ የአፍሪካ ጉባኤ ተደርጓል።

በዚህም ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመጣውን ሁለንተናዊ ለውጥ በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡

“አፍሪካ ሊደርሺፕ መጋዚን” በተለያዩ ዘርፎች ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች በየዓመቱ የሽልማት መርሐ ግብር በማዘጋጀት እውቅና የሚሰጥ መሆኑን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ባለፉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው የለውጥ ስራዎች መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ሀገር በቀልና የውጭ ተቋማት ከ30 በላይ ሽልማቶች መበርከታቸው የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.