Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በሩሲያው ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ንግድ ትርኢት ላይ ተሳተፈች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ2023 የሩሲያው ዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ንግድ ትርኢት ላይ መሳተፏን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የንግድ ትርዒቱ ዘላቂ ምርትና ምርታማነትን እንዲሁም የማሻሻያ ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም ለከተሞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች በብረት ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂዎች፣ ለኃይል አቅርቦት ዘርፍ የሚሆኑ ቴክኖሎጂዎች፣ በትራንስፖርት ኢንጂነሪንግ፣ ለአዳዲስ ምርቶች፣ ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ ችግር ፈቺ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም የሕክምና መሳሪያዎችና ቴክኖሎጂዎችን በማምረት ላይ አጀንዳውን እንዳደረገም ተገልጿል፡፡

በመርሐ ግብሩ የኢንዱትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም አመት የዘለቀውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ በኢንቨስትመንት ለማጠናከር እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ሀገር ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ የሩሲያ ባለሃብቶች ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሩሲያው ጠቅላይ ሚኒስትር ሚካሂል ሚሹስቲን በበኩላቸው÷ አውደ ርዕዩ በርካታ የልምድ ልውውጦች እና ቁልፍ የሆኑ ዘርፎች ለማዳበር ያግዛል ብለዋል፡፡

በዚህም በኢንዱስትሪ፣ በቴክኖሎጂ እና በፈጠራዎች ላይ አጋር ግንኙነቶችን ለማዳበር ዝግጁ ነን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ከ16 ሀገራት የተውጣጡ ልዑካን እንደተሳተፉ እና የንግድ ትርኢቱ በተለያዩ የሩሲያ ግዛቶች ለእይታ እንደሚበቃ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.