Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ የኢትዮ-ኬንያ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮ-ኬንያ ሁለንተናዊ ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር እየተሠራ መሆኑን ገለጹ።

አቶ ደመቀ ነገ እና ከነገ በስቲያ በሚካሄደው 43ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አሥፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ኬንያ ናይሮቢ መግባታቸው ይታወቃል።

በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተዘጋጀ ሥነ-ሥርዓት ላይ አቶ ደመቀ ባደረጉት ንግግር÷ ሁለቱ ሀገራት በጋራ  ለአፍሪካ ቀንድ ሠላምና ልማት ይሰራሉ ብለዋል።

የኤምባሲው አመራር እና መላው ሰራተኞች ለግንኙነቱ መጎልበት ጠንክረው እንዲሰሩም አሳስበዋል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ በበኩላቸው÷ የኤምባሲው አባላት የተሰጣቸውን የመንግስት እና የሕዝብ ተልዕኮ ለመወጣት በትጋት እየሠሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በኤምባሲው ከተዘጋጀው ሥነ ሥርዓት ቀደም ብሎ አቶ ደመቀ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.