Fana: At a Speed of Life!

በባሕርዳር በ650 ሚሊየን ብር የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር በ650 ሚሊየን ብር የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመርቋል።

የባሕርዳር ከተማ የንጹህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ከጃፓን መንግሥት ባገኘው 650 ሚሊየን ብር ድጋፍ ነው የተገነባው፡፡

በምረቃ መርሐ ግብሩም የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) እና የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በሰከንድ 339 ሊትር ውኃ የሚያመነጩ 9 ጉድጓዶችን ያስተሳሰረ 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ሊትር ውኃ ማጠራቀም የሚችሉ ጋኖችን እንደያዘም ነው የተገለጸው።

ለ147 ሺህ የከተማዋ ነዋሪዎችም አገልግሎት እንደሚሰጥ አሚኮ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.