Fana: At a Speed of Life!

22ኛው የዋና ኦዲተሮች ዓመታዊ ጉባዔ በቦንጋ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የዋና ኦዲተሮች ዓመታዊ ጉባኤ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል፡፡

መንግስት ለክልሎች የሰጠውን የድጋፍ እና ድጎማ በጀት የነጠላ ኦዲት አፈጻጸም በጉባዔው መገምገሙ ተገልጿል።

ከክልልና ከከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች ጋር ያለው ግንኙነትና በቀጣይ ለሚካሄደው የዋናው ኦዲተር ጉባዔ አጀንዳ የሚቀርጽ ኮሚቴ ማዋቀር ላይ ምክክር መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

በጉባዔው፥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር መሰረት ዳምጤ እንዲሁም የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.