Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ የቻድ አቻቸውን በመልስ ጨዋታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቻድ አቻውን በመልስ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በ2024 ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከቻድ አቻው ጋር ጨዋታውን አድርጎ 6 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

ዛሬ የመልስ ጨዋታ የተደረገ ሲሆን÷ በጨዋታው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የቻድ አቻውን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ግቦቹን ሎዛ አበራ በ11ኛው ደቂቃ፣ ሴናፍ ዋቁማ በ20 እና በ45ኛው ደቂቃ፣ቱሪስት ለማ በ89ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.