Fana: At a Speed of Life!

አረንጓዴ አሻራ በአርብቶ አደሩ አከባቢ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ተጋላጭነትን ከመቀነስ አኳያ ሚናው ከፍተኛ ነው – ርእሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰቱ ያሉትን ችግሮች ለመግታት እና በተለይም አርብቶአደሩ አካባቢ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ሚናው ከፍተኛ ነው ሲሉ ተናገሩ።

ርእሰ መስተዳድሩ እንደ ሀገር በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብርን በክልል ደረጃ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አስጀምረዋል።

የአረንጓዴ አሻራ የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን አቶ አወል ተናግረዋል።

በከፍተኛ ደረጃ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመግታት በተለይም በአርብቶአደሩ አካባቢ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የድርቅ ተጋላጭነት ለመቀነስ መርሐ ግብሩ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

ያለፉት ጊዜያትም ሆነ በዛሬው ዕለት የምንተክላቸው ችግኞች የዛሬ ችግኝ የነገ ምግብ፣ ጥላ እና ውበት መሆናቸውን ተገንዝበን የተከልናቸው ችግኞች መንከባከብ የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው ሲሉ ማሳሰባቸውን የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.