Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳተፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት እንደ ሀገር 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣የግብርና ሚኒስቴር፣የጤና ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞ በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት እንዲሁም ሌሎች ተቋማት በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

የተቋማቱ አመራሮች እና ሰራኞች በተለያዩ አካባቢዎች ለችግኝ ተከላ በተመረጡ ቦታዎች በመገኘት ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያኖሩት፡፡

እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀንበር 500 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.