Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የተፈጥሮ ሀብትን በማልማት የህዝብን ህይወት ለመለወጥ መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም በማስጠበቅና የተፈጥሮ ሀብቱን በማልማት የህዝብን ህይወት ለመለወጥ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተናገሩ።

ባለፉት 11 ተከታታይ ቀናት በ11 ዘርፎች ሲካሄድ የነበረው የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የድጋፍና ክትትል ቡድን የማጠናቀቂያ ውይይት ተካሂዷል።

የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሰጡት አስተያየት÷ የጋምቤላ ክልል እምቅና ያልተነካ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት መሆኑን በቆይታቸው ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል።

ይሁን እንጅ በክልሉ ያለውን ፀጋ ወደ ልማት በመለወጥ የሕዝቡን ኑሮ ለማሻሻል ጅምር ስራዎች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆናቸውን አብራርተዋል።

በክልሉ ያለውን ሀብት ሙሉ በሙሉ ማልማት ቢቻልም ከክልሉ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ ሀብት መኖሩን ጠቁመው ያለውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው÷ የተሰጡትን ምክረ ሃሳቦች በመውሰድ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

የክልሉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግም አመራሩ ከህብረተሰቡ ጋር እየሰራ መሆኑን መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.