Fana: At a Speed of Life!

ከቡና ምርት ጋር በተያያዘ በዐውደ-ርዕዮች በተደረገ ተሳትፎ ከ76 ሚሊየን በላይ ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 141 ቡና ላኪዎች እና የቡናና ሻይ ባለስልጣን በተለያዩ ዐውደ-ርዕዮች ተሳትፈው 76 ሚሊየን 500 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

ገቢው የተገኘው በዐውደ-ርዕዮቹ ላይ 47 ሺህ 424 ቶን ቡና ውል (ኮንትራት) በመግባት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ሕገ-ወጥ የቡና ንግድን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ተወርሶ ለሽያጭ የቀረበ የቡና መጠን እና የግብይት ጊዜን በመተላለፍ ከ192 ሚሊየን 766 ሺህ በላይ ብር የተሰበሰበ ቅጣት ለመንግሥት ገቢ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ240 ሺህ 369 ቶን በላይ ቡና ወደ ውጪ ገበያ ተልኮ ከ1 ነጥብ 3 ቢሊየን በላይ የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱ ይታወቃል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ360 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጭ በመላክ 1 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

በዚህም ወደ ውጭ ከተላከው የቡና ምርት የተገኘው ገቢ ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ቅናሽ ማሳየቱ ነው የተመለከተው፡፡

ይሁን እንጅ ከዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ መቀነስ እና ሌሎች ፈታኝ ሁኔታዎች አንጻር አፈጻጸሙ አበረታች መሆኑ ተገልጿል፡፡

የተላከው ቡና በመዳረሻ ሀገራት ሲታይ ሳዑዲ ዓረቢያ በገቢ÷ 17 በመቶ፣ ጀርመን 13 በመቶ እንዲሁም አሜሪካ 11 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገባቸው ተጠቁሟል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.