Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ከ836 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በክረምት ስንዴ ተሸፍኗል – ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2015/2016 የምርት ዘመን ከ836 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት በክረምት ስንዴ መሸፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ።

ክልሉ በ2015/2016 ዓ.ም ምርት ዘመን 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በክረምት ስንዴ ለመሸፈን ማቀዱን ገልጸው፥ እስከ አሁን 836 ሺህ 186 ሄክታር መሬት ላይ ስንዴ መዘራቱን ጠቁመዋል።

በምርት ዘመኑ በስንዴ የሚሸፈነው ማሳ ከ2014/15 የምርት ዘመን አንጻር የ500 ሺህ ሄክታር ብልጫ እንዳለው ጠቅሰዋል።

በተያዘው ክረምት በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ በክላስተር እየለማ የሚገኘው የስንዴ ቡቃያ በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያሰፈሩት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.