Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክ/ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በ2015 በጀት ዓመት የተገነቡ ልዩ ልዩ 65 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

ዛሬ የተመረቁት 41 ፕሮጀክቶች በመደበኛ የመንግስት የካፒታል በጀት የተገነቡ ሲሆኑ ፥ 24 ደግሞ በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው ተብሏል፡፡

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ከሚመልሱና የኑሮ ሸክሙን ከሚያቀሉ ፕሮጀክቶች መካከልም ትምህርት ቤቶችና የጤና ጣቢያዎች ግንባታና ማስፋፊያ፣ የአስተዳደር ሕንጻዎች ፣ ፖሊስ ጣቢያ፣ ዳቦ ፋብሪካና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ይገኙባቸዋል::

ምክትል ከንቲባና የስራ ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ከተማ አስተዳደሩ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለሚሰጡ ፕሮጀክቶች የላቀ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛው በጀት ለካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ ተመድቧል::

ሕዝቡ ችግሮቹን ለመፍታት ከመንግስት ጎን በመሆን በአካባቢ ልማትና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የተመረቁት ፕሮጀክቶች ማሳያ እንደሆኑ ከከተማው ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተገነቡ ግንባታዎች ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ሕዝቡ በባለቤትነት ሊንከባበከባቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.