Fana: At a Speed of Life!

በ500 ሚሊየን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገበት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት ተመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ500 ሚሊየን ብር ወጪ ማስፋፊያ የተደረገበት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሰተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክትን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

አቶ ሙስጠፌ መሀመድ÷ ሆስፒታሉ በተለይ ለተለያዩ የህክምና አገልግሎቶች ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ውጪ ሀገራት የሚላኩ ታካሚዎች አገልግሎቱን በሆስፒታሉ እንዲያገኙ እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ÷ የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ክፍሎችና የአምቡላንስ ጥሪ ማዕከላት መስፋፋቱ በተለይ በድንገተኛ አደጋ ሳቢያ የሚከሰት ሞትን ለመቀነስ ሚናው የጎላ ነው ማለታቸወን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱላሂ ሁሴን÷ ሆስፒታሉ በክልሉ ያለውን የጤና ተደራሽነት እና ጥራት በማሳደግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

ማስፋፊያው 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ የድንገተኛ አምቡላንስ አገልግሎት ማዕከል፣ 30 የህክምና አልጋዎች ያሉት የድንገተኛ እና ፅኑ ህክምና ማዕከል እና የኤም አር አይ አገልግሎትን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.