Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዳባ ደበሌ በጃፓን የሩዋንዳ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ  አምባሳደር ዳባ ደበሌ በጃፓን የሩዋንዳ አምባሳደር ኤርነስት ሩዋሙሲዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ አምባሳደሮች በጃፓን ቆይታቸው ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በቅንጅት ለመስራት መስማማታቸውን ከጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ  አምባሳደር ዳባ ደበሌ ለጃፓን ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ናሩሂቶ በንጉሠ ነገሥት ቤተ-መንግሥት በመገኘት የሹመት ደብዳቤያቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.