Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር 20ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር 20ኛውን ዓለም አቀፍ ጉባዔ ማካሄድ ጀመሯል።

በጉባኤው መክፈቻ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ ከሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እና የድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ማህበሩ በአሁኑ ጉባዔው በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በተለያዩ ክፍለ ኢኮኖሚዎች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን ይመለከታል ተብሏል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ እንዳሉት÷ ኢኮኖሚውን ለማሻሻል በርካታ ቀሪ የቤት ስራዎች አሉ።

አለም አሁን እያጋጠመው ያለው የዋጋ ግሽበት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳጊ ሀገራት ፈተና መሆኑንም ጠቅሰው፤ ይህንን ለመቋቋምም ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ፎረም ጋር በትብብር መስራት ይጠይቃል ነው ያሉት።

ጉባኤው በሚኖረው ቆይታ የማህበሩ አባላትና ተጋባዥ ምሁራን በሚያቀርቧቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ውይይት ያካሂዳል።

ማህበሩ ከምጣኔ ሀብት ጋር በተያየዙ ጉዳዮች ጥናት በማድረግም ለፖሊሲ አውጭ አካላት ምክረ ሀሳብ ያቀርባል ተብሏል።

በምንይችል አዘዘው እና ሲሳይ ዱላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.