Fana: At a Speed of Life!

ተመራቂዎች ዕውቀትን ለመቅሰም የተጓዙበትን ጥበብና ጥረት በሀገር ግንባታው መድገም አለባቸው – ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራቂዎች ዕውቀትን ለመቅሰም የተጓዛችሁበትን ጥበብና ጥረት በሀገር ግንባታው ሂደትም በንቃት በመሳተፍ ስኬታችሁን ማስቀጠል አለባችሁ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ገለጹ።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በዶክትሬት ዲግሪ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን ከ7 ሺህ 630 በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ስኬት የሚመዘገበው በበርካታ ልፋትና ድካም መሆኑን ገልጸዋው፤ ለዚህም ተመራቂዎች ማሳያ ናችሁ ብለዋል።

“ባለፉት ዓመታት በኮሮና፣ በጦርነትና በሌሎች ችግሮች ምክንያቶች ሳትደናቀፉ ለዛሬዋ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” በማለት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተመራቂዎች በትምህርት ዕውቀትን ለመቅሰም የተጓዙበትን ጥበብና ጥረት በሀገር ግንባታው ሂደትም በንቃት በመሳተፍ ስኬታቸውን ማስቀጠል እንዳለባችው አስገንዝበዋል።

በመምህራኖቻቸውና በራሳችው ጥረት ያገኙትን በተግባር የተደገፈ ዕውቀት ለሀገራቸው ልማትና ሰላም ግንባታ በማዋል ችግር ፈቺ እንዲሆኑም አሳስበዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች ሀገሪቱ አሁን ካለችበት ችግር በማውጣት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቀሰሙት ዕውቀት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸውም በአፅንኦት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.