Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 3ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን አድርጎ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

ካቢኔው መጀመሪያ የተወያየው የኑሮ ውድነቱን ጫና ለመቀነስና ገበያውን ለማረጋጋት እንዲቻል የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ሥራዎች ድርጅትን ለማቋቋም ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

በመቀጠል የዳግማዊ ሚኒልክ የሕክምናና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደገና ለማቋቋም ተዘጋጅቶ በቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መዋቅራዊ ፕላን የፀደቀበት አዋጅ ቁጥር 48/2009 በሚያዘው መሰረት ተጠንተው በቀረቡ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የፕላን ማሻሻያዎች መዋቅራዊ ፕላን መነሻ በማድረግ የአካባቢ ልማት ፕላን በማዘጋጀት በከተማዋ በተለዩ ቦታዎች የመንገድ ትስስርን ፣ ጥግግትን፣ የከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ቦታዎችን ማሻሻልን፣ የህፃናት የመጫወቻ ቦታዎችን ማስፋፋትን እና የከተማዋን ውበት የሚጨምሩ ሌሎች ፕላኖችን ለማሻሻል በቀረበው ጥናት ላይ ተወያይቶ ጥናቱን ተቀብሎ አፅድቋል፡፡

ይህም ከተማዋን በፕላን እንድትመራ በማድረግ ጉልህ ሚና የሚጫወት ይሆናል መባሉን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.