Fana: At a Speed of Life!

ሻምበል አበበ ቢቂላ የሀገር ኩራት ምንጭ እና ፈርጥ ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ሻምበል አበበ ቢቂላ የሀገር ኩራት ምንጭ እና ፈርጥ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጣሊያን መዲና ሮም ጎዳና ለአትሌት አበበ ቢቂላ ማስታወሻ አኑረዋል።

ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ሻምበል አበበ ቢቂላ የሀገር ኩራት ምንጭ እና ፈርጥ ነው”ብለዋል።

በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ለዘመናት የኢትዮጵያን ስም ያስነሣ እና ለአፍሪካውያን አትሌቶች በር የከፈተ ዕንቁ ሯጭ ነው ሲሉም አስፍረዋል።

አትሌቱ  የጽናትና የአይበገሬነት ተምሳሌት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ጣልያን ሮም ከተማ በስሙ የተሰየመ ጎዳና  አለው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በስፍራው የእርሱን ማስታወሻ አኑረናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.