Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሔድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 9ኛ የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ ለ3 ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ መሰረትም የበጀት ዓመቱ የክልሉ መንግስት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተጠቁሟል።

ምክር ቤቱ በክልሉ የመልካም አስተዳደር፣ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳይ ላይ የተሠሩ ሥራዎችንም በትኩረት ይመለከታል ተብሏል።

በተጨማሪም የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት ተጨማሪ በጀት እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ተጠቅሷል።

የክልሉ ምክር ቤት ቤት ምክትል አፈጉባኤ ዓለምነሽ ይባስ በጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት÷ በክልሉ አሁን ላይ የታየውን ሠላም በመጠቀም በሕዝቡ የሚነሱ የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ የበለጠ መሥራት ይገባል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.