Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው በሀገር ቤት የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው በሀገር ቤት የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ በደቡብ አፍሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የተውጣጣ ልዑካን ቡድን በደቡበ አፍሪካ የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የልማት ተቋማት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡

በወቅቱም በሃውቴንግ ፕሮቪንስ፤ ዌስትራንድ – ራንድፎንቴይን በሚገኘ የዳያስፖራ የቢዝነስ ማዕከል የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ማዕከሉ በከፍተኛ ካፒታል የሸቀጣ ሸቀጥ ማከፋፊያ ቢዝነስ ዘርፍ ለኢትዮጵያውያንና ደቡብ አፍሪካውያን የሥራ ዕድል የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።

የልዑካን ቡድኑም ተቋሙ እያከናወነ ያለው ተግባር የሀገርንና የዜጎችን መልካም ገጽታን ከፍ ያደረገና ለሌሎችም በተምሳሌትነት የሚወሰድ ነው ማለታቸውን የዳስፖራ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡

በወቅቱም አምባሳደሩ ባስተላለፉት መልዕክት÷በሀገር ውስጥ መንግስት ለዳያስፖራው ያመቻቻቸውን የኢንቨስትመንትና የቢዝነስ አማራጮች በመጠቀም ወደ ስራ የገቡ ዳያስፖራዎችን አመስግነዋል፡፡

የዳያስፖራ አባላትና ተቋማት በሀገር ቤት ያላቸውን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲያሳድጉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.