Fana: At a Speed of Life!

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ሪች ላንድ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋል (ዶ/ር) በባሕርዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ሪች ላንድ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የግንባታ ሒደትን ጎብኝተዋል፡፡

ፋብሪካው በዋናነት የበቆሎ ሰብል ምርትን በግብዓትነት በመጠቀም ÷ የቢራ ብቅልን የሚተካ ምርት እንዲሁም ግልኮስ፣ ማካሮኒ፣ የምግብ ዘይትን ጨምሮ ሌሎች ምግብ ነክ ምርቶችን ያመርታል ተብሏል።

ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ሪች ላንድ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከኢንዱስትሪ ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር ለኢኮኖሚያችን እድገት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ግንባታው ተጠናቆ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ አሁን ካለበት የግንባታ ፍጥነት በተሻለ መንገድ ለመፈጸም በቂ የሰው ኃይልና ግብዓት አሟልቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዘርፉን ተወዳደሪነት ለማሳደግ የክልሉ መንግስት ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.