Fana: At a Speed of Life!

መንግስት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚሹ 4 ሚሊየን ዜጎች ድጋፍ ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚሹ አራት ሚሊየን ዜጎች በራሱ አቅም ድጋፍ ማቅረብ መጀመሩን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የሎጅስቲክ ኦፕሬሽን ስራ አመራር ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ደምሴ÷ ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ከተቀመጠው ክምችት ላይ 115 ሺህ ኩንታል ሩዝ፣ ዱቄትና እህል እርዳታ ለሚሹ ዜጎች እየተሰራጨ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም 2 ሚሊየን ሊትር ዘይት እና ከ60 ሺህ ኩንታል በላይ አልሚ ምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች መላኩን ጠቁመዋል፡፡

የሰብዓዊ እርዳታው ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ በ56 ተሽከርካሪዎች መጓጓዝ መጀመሩን ነው የተናገሩት፡፡

ድጋፉ በሁሉም ክልሎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ተደራሽ እንደሚሆን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል፡፡

በማህሌት ተ/ብርሃን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.