Fana: At a Speed of Life!

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ገለጻ ተደረገላቸው

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፈተናውን የሚወስዱ የማኅበራዊ ሣይንስ ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባታቸው ይታወቃል።

ተማሪዎቹ ከነገ ጀምሮ የሚሰጣቸውን ፈተና እና ተቋማዊ ዝግጁነትን በተመለከተ በዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችና በትምህርት ሚኒስቴር በተወከሉ አስተባባሪዎች አማካኝነት ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች አጠቃላይ ተቋማዊ ዝግጁነትን የተመለከተ ማብራሪያ ያደረጉ ሲሆን÷ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አስተባባሪዎች ደግሞ የፈተና መመሪያና ደንቦችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ተማሪዎቹ ፈተናውን ተረጋግተው እንዲፈተኑም ሥነ ልቦናዊ ዝግጅትን የሚያጠናክሩ ምክሮችም ተሰጥተዋል።

ፈተናው ከሐምሌ 19 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.