Fana: At a Speed of Life!

በ2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለ400 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ለ400 ሺህ ዜች የሥራ ዕድል ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

በቢሮው የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀምና የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር ዓባይ እና ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የዘርፍ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ አምራቾችን በመደገፍ ፣ የመስሪያ ቦታዎችን በማቅረብ ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠርና በተቋም ግንባታ ላይ ቢሮው ሲሰራ መቆየቱን ተገልጿል፡፡

በበጀት ዓመቱ የተሻለ የሥራ አፈፃፀም ለነበራቸው ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች የእውቅናና ሽልማት ይሰጣል መባሉን የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.