Fana: At a Speed of Life!

የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚያግዙ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ16 ሺህ ህመሙ ባለባቸው ሰዎች ላይ በተደረገ ሙከራ ሁሉም የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የደም ግፊትን እንደሚቀነሱ በብሪቲሽ ጆርናል ኦፍ ስፖርት ሜዲስን ላይ የታተመ ጥናት ውጤት አመላክቷል፡፡

መሬት ላይ በደረት በመተኛት በትክሻ ትይዩ በክርን መሬትን በመደገፍ ለሁለት ደቂቃ መቆየት (Planks) ከኤሮቢክስ ስፖርት በተለየ ሁኔታ ደም ግፊትን እንደሚቀንስ ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም ግድግዳ በመደገፍ እና ከመሬት 60 ሴንቲ ሜትር ርቀት ላይ ከጉልበት ሸብረክ ብሎ እጆችን ወደፊት በመዘርጋት ለሁለት ደቂቃ መቆየት (wall squat) የደም ግፊት ህመምን በተለየ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የስፖርት አይነቶች በሚሠሩበት ወቅት ከኤሮቢክስ ስፖርት በተለየ የሰውነት ክፍሎች እንዲጨናነቁ በማድረግ ደም በቀላሉ እንዲዘዋወር ስለሚረዱ የደም ግፊትን ይቀንሳሉ ነው የተባለው፡፡

ከፍተኛ የደም ግፊት÷ በደም ስሮች፣ በልብ እና ሌሎች የአካል ክፍሎች ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት ለተለያዩ ህመሞች ያጋልጣል፡፡

የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች÷ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እንዲያዘወትሩ፣ የአመጋገብ ሥርዓታቸው ጠየናማ እንዲሆን፣ አልኮል እንዳይጠጡ እና ሲጋራ እንዳያጨሱ ይመከራል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.