Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ተወካይ ክሪስ ኒኮል ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች በድርጅቱ በኩል የተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ የሚተገበሩ ስራዎችን አንስተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ እርዳታ ለሚፈልጉ ዜጎች በቀዳሚነት ሰብዓዊ  ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልፀው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ለሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የክልሉ መንግስት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡

አሁንም የእለት ደራሽ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በርካታ ዜጎች መኖራቸውን የጠቆሙት ርዕሰ መስዳድሩ ሌሎች ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ተወካይ እና ካንትሪ ዳይሬክተር ክሪስ ኒኮል በበኩላቸው÷ ድርጅታቸው ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሰብአዊ እርዳታ ሲያቀርብ መቆየቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም የዓለም ምግብ ፕሮግራም በክልሉ  ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.