Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል 618 ሺህ ሄክታር በበልግ የስንዴ ምርት መሸፈኑን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2015 ዓ.ም የምርት ዘመን 618 ሺህ ሄክታር መሬት በበልግ የስንዴ ምርት መሸፈኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡

በ2015 ዓ.ም የምርት ዘመን በበልግ ስንዴ ምርት የተሸፈነው÷ በቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክልሉ መንግስት  የአርብቶ አደሩን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ እየሠራ መሆኑን አቶ ሽመልስ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

በተለይም በተደጋጋሚ እያጋጠመ ላለው የድርቅ ችግር ጊዜያዊ መፍትሔ ከማበጀት ጎን ለጎን ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ  እየተሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የአርብቶ አደሩ የኑሮ ዘይቤ የሆነውን የከብት እርባታ ስራ ከማሻሻል ጎን ለጎን በአካባቢው የሚገኘውን መሬት ወደ ልማት ለማስገባት በተደረገው ጥረት በስንዴ ልማት አዲስ ታሪክና ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አመላክተዋል።

በቀጣይም መንግስት የክልሉን ግብርና ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ  አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.