Fana: At a Speed of Life!

ዓለማቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ ሽልማትን ያሸነችው ኢትዮጵያዊ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊቷ ፈትያ ዖስማን ዓለማ አቀፉ የተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ ኀብረት የሚያዘጋጀውን የጥብቅ ሥፍራዎች ጠባቂ ጓዶች ሬንጀርስ ሽልማት አሸናፊ ሆናለች።

ዋና ፅሕፈት ቤቱ ስዊዘርላንድ  ግላንድ ከተማ ውስጥ የሆነው ይሕ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃና እንክብካቤ ኀብረት በዘንድሮ መርሐ ግብሩ ከዓለም ዙሪያ ተመልምለው  የሚያከናውኑት ተግባር ይበልጥ ውጤታማ ነው ያላቸውን ዘጠኝ ቡድኖችና ግለሰቦችን ዕውቅና ሰጥቶ ሸልሟል።

ከነዚህም  ቡድኖችአንዷ የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ሥፍራ የሬንጀርስ መሪ የሆነችው ፈትያ ዖስማን ትገኝበታለች።

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ከሚሰሩ ሬንጀርስ መካከል ሴት የቡድኑ አባል ፈቲያ ብቻ የነበረች ሲሆን ÷በዝሆኖቹ መጠለያ ሥራ ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ያሳየችው ብቃት 60 አባላት ያሉትን የጥብቅ ሥፍራው ሬንጀርስ ጏላፊ እንድትሆን አስችሏታል።

በአመራሯም በጥብቅ ሥፍራውና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል የሚከሰቱ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የማድረግ ብቃቷ ሌላኛው ለሽልማት ካበቋት ምክንያቶች ሆኖ ተጠቅሶላታል።

በፆታ ሰበብ የሚደርሱ ጫናዎች ሳይበግሯት ለሌሎች ሴቶችም ዓርአያ እስከመሆን መድረሷም ለዓለማቀፍ ሽልማቱ ካበቋት  ምክንያቶች መካከል  አንዱ ነው ተብሏል።

ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በተካሄደው በዚሁ ዓለም አቀፍ የዕውቅና መርሐ ግብር ከኢትዮጵያዊቷ ፈቲያ በተጨማሪ ከደቡብ አፍሪካ ከኮሎምቢያ ፣ከሜክሲኮና ከሌሎች ሀገራት በአጠቃላይ ዘጠኝ ቡድኖች እና ግለሰቦች ተሸላሚ ሆነዋል።

በቡድን አልያም በተናጠል በስም ለዕውቅና የበቁት እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ዶላር መሸለማቸውንም ኀብረቱ ገልጿል።

ዓለማቀፉ የጥብቅ ሥፍራዎችና ብዝሓ ህይወት ጥበቃና እንክብካቤ ኀብረት ከተመሠረተ 74 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡

 

በተስፋየ  አለነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.