Fana: At a Speed of Life!

በሎጂስቲክሱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት በጥናት የተደገፈ አሰራር እየተተገበረ መሆኑ ተመለከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሎጂስቲክሱ ዘርፍ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታት በጥናት የተደገፈ አሰራር እየተተገበረ መሆኑ ን የኢትዮ-ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማህበራት ፕሬዚዳንት ኤልሳቤጥ ጌታሁን ገለጹ፡፡

“የተሳለጠ የኢትዮ-ጅቡቲ መስመር፣ ለቀልጣፋና አዋጪ ሎጂስቲክስ አገልግሎት” በሚል መሪ ሀሳብ የሎጂስቲክስ ዘርፉን ማጠናከር ያለመ የምክክር መድረክ አየተካሄደ ነው።

የማህበሩ ፕሬዚዳንት ኤልሳቤጥ ጌታሁን ÷ኢትዮጵያ የተሳለጠ የሎጂስቲክስ አገልግሎት እንዲኖራትናት ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም የወጪ እና ገቢ እቃዎች የወደብ ላይ ቆይታቸውን በማሳጠር በፍጥነት ለተፈለገው አላማ እንዲውሉ የኢትዮ ጅቡቲ መስመር የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር አየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ዴጌ ቦሩ በበኩላቸው ÷ የኢትዮጵያ የሎጅስቲክስ ዘርፍ በርካታ ማነቆዎች እንዳሉት ጠቅሰዋል፡፡

ለአብነትም በቂ የመሰረተ ልማ እና የተጠናከረ የፋይናንስ ድጋፍ አለመኖር እንዲሁም በቂ የሰለጠነ የሰው ሃይል አለመኖር ለአብነት የሚነሱ ችግሮች ናቸው ብለዋል።

እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም መንግስት ከማህበራት እና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑ ነው ያነሱት፡፡

በኢትዮ-ሎጂስቲክስ ዘርፍ ማህበራት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በሳሙኤል ወርቃየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.