Fana: At a Speed of Life!

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በሀገርቀፍ ደረጃ ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በሀገርቀፍ ደረጃ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና በሁሉም ፕሮግራሞች እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ይህንንም ወጥ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም እንዲቻል ለሁሉም የግልና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በተጻፈ ደብዳቤ መገለጹን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎቹ የ2016 ትምህርት ዘመን የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ማስታወቂያ በማዉጣትና በመመዝገብ እጩ ተማሪዎችን እስከ መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲያሳዉቁ መልዕክት መተላለፉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.