Fana: At a Speed of Life!

ሂጅራ ባንክ አዲስ መተግበሪያ ሥራ ላይ አዋለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሂጅራ ባንክ “ኦምኒ ፕላስ” የተሰኘ አዲስ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል፡፡

የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት ታስቦ ሥራ ላይ የዋለው መተግበሪያ በ 5 ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ በመቅረቡ÷ ለተጠቃሚው ቀላልና ምቹ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ዩ ኤስ ኤስ ዲ-የሞባይል ባንኪንግና-የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎቶችን በአንድ ፕላትፎርም ያዋሃደ መተግበሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የባንኩ ደንበኞች መተግበሪያውን ከ “ፕሌይ ስቶር” ወይንም ከ “አፕ ስቶር” በማውረድ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ተብሏል፡፡

መተግበሪያውን በመጠቀም ደንበኞች የገንዘብ መጠን ከመቆጣጠር ባሻገር በሂጅራ ባንክ ውስጥ ባሉ አካውንቶች መካከል ወይም ወደ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ቀሪ ሂሳብ ማወቅና የሂሳብ ሪፖርት ማግኘት እንደሚችሉ ተመላክቷል፡፡

ከሂጅራ ባንክ ወደ ቴሌ ብር ገንዘብን ማስተላለፍ፣ የሂሳብን መረጃ ማውረድና ለሌሎች ማጋራት እንዲሁም የአየር ሰዓት መግዛትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚቻል ነው የተገለጸው፡፡

መተግበሪያው ጥሬ ገንዘብ መቀበል የሚያስችል መሆኑም ባንኩ አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.