Fana: At a Speed of Life!

ለታዳጊ ሀገራት የሚደረገው የልማት ፋይናንስ በቂና ፍትሃዊ አይደለም – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለታዳጊ ሀገራት የሚደረገው የልማት ፋይናንስ በቂና ፍትሃዊ አለመሆኑ አሁንም እንደቀጠለ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አመለከቱ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ በተካሄደውን የዘላቂ ልማት ግቦች አፈጻጸም ጉባዔ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸው እንዳነሱት፥ በዘላቂ ልማት ግቦች አፈፃፀምና በአዲስ አበባ የድርጊት መርሐ ግብር አጀንዳ ላይ ያለው ቁርጠኝነት ጉድለት አለበት።

የሀገር ውስጥ ሃብት የማሰባሰብ ስራ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተዳከመ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አክለውም ፥ ለታዳጊ ሀገራት የሚደረገው የልማት ፋይናንስ በቂና ፍትሃዊ አለመሆኑ እስካሁን ቀጥሏልም ነው ያሉት።

የዓለም የፋይናንሺያል አርክቴክቸር ማሻሻያ እንዲደረግ የጠቆሙት አቶ ደመቀ፥ ሀገራትና ተቋማት እዳ ስረዛ ላይ ሥር ነቀል እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ የድርጊት መርሐ ግብር አጀንዳ በ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችል የአፈጻጸም ሂደት እንዲኖር በፈረንጆቹ 2015 በተመድ የተቀረጸ መሆኑ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም አቶ ደመቀ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፒ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia #UN #SDGs #US

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.