Fana: At a Speed of Life!

የቀይ ባህር ተለዋዋጭ የደኅንነት ጉዳዮችና ቀጣናዊ ትብብር ላይ ያተኮረ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀይ ባህር ተለዋዋጭ የደኅንነት ጉዳዮችና ቀጣናዊ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ትብብር የተዘጋጀው ጉባዔ÷ “የቀይ ባህር የደኅንነት ሁኔታ፤ ቀጣናዊ ምክክርና ትብብር መልክዓ-ፖለቲካዊ መጠላለፍ በበዛበት ዓለም” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የሚካሄደው።

ጉባኤው የቀይ ባህር ተለዋዋጭ የደኅንነት ጉዳዮችና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት አግባብ ላይ የሚመክር መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቀጣናው አሁን ያሉ የጸጥታ ሥጋቶች በቀይ ባህር ደኅንነት ሊኖረው ስለሚችለው ተጽዕኖና መፍትሔዎች ላይ እንደሚያተኩርም ተጠቁሟል፡፡

የቀጣናው ሀገራት ተቀራርበው የሚሰሩበትና ጠንካራ፣ ሁሉን አቀፍና ከሁኔታዎች ተለዋዋጭነት ጋር አብሮ የሚሄድ ቀጣናዊ የጸጥታ ትብብር ማዕቀፎችን ለመፍጠር በሚያስችሉ የፖሊሲ አማራጮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ÷ ጉባኤው የአካባቢው ሀገራት የጸጥታ ሥጋቶችን በጋራ ለመፍታት በትብብር መሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.