Fana: At a Speed of Life!

አንቶኒዮ ጉተሬዝ ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመወጣት ለባለብዙ ወገን ተቋማት ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመወጣት ለባለብዙ ወገን ተቋማት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተቋማት ዓለም ያለበትን ሁኔታ ካላንጸባረቁ ችግሮችን በብቃት መፍታት እንደማይቻል ገልጸው፤ ተቋማቱ ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር በመጓዝ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።

ተቋማት ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ የችግሩ አካል የመሆን ስጋት አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ዓለም ባለመረጋጋት ውስጥ እየዋዠቀች ነው በማለት የገለጹት ዋና ፀሐፊው፤ በየቀጣናው ፖለቲካዊ ውጥረቶች መጨመራቸውንና ዓለም ዓቀፋዊ ተግዳሮቶች እየበረቱ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስና የቴክኖሎጂ የጎንዮሽ ጉዳት ዓለም ፈታኝ ሁኔታዎችን እንድትጋፈጥ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የታዩት ችግሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈትተው ወደ አንድነት መምጣት ተችሎ እንደነበር አስታውሰው፤ አሁን ላይ ግን ዓለም በፍጥነት እየተነጣጠለ ነው ብለዋል፡፡

በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ አውሮፓ በመድብለ ፖለቲካ ብዙ ሀይሎች እንደነበሯት ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ ነገር ግን ጠንካራ የባለብዙ ወገን ተቋማት ባለመኖራቸው ውጤቱ የአንደኛው የዓለም ጦርነት ነበር ብለዋል።

በመሆኑም ዓለምን እየፈተኑ ለሚገኙ ችግሮች ምላሽ ለመስጠት የመድብለ ፖለቲካ ዓለም ጠንካራ እና ውጤታማ የባለብዙ ወገን ተቋማት ያስፈልጋል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.