Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ‘ዮዮ ጊፋታ’ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ ‘ዮዮ ጊፋታ’ በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በወላይታ ሶዶ ከተማ ተከበረ።

በበዓሉ ስነ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

የዮዮ ጊፋታ በዓል በአብሮነትና በመተጋገዝ እንዲሁም በተለያዩ ክንውኖች ደምቆ እየተከበረ ነው።

በዓሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመቻቻል፣ የደስታና የተድላ እንዲሆን የሀገር ሽማግሌዎች መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ መርቀዋል።

የባህል፣ ቋንቋ፣ ወግና የታሪክ እሴትን ማክበርና መንከባከብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በወላይታ ብሔር ዘንድ ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ ዘመን መሸጋገሪያ ብሥራት ተደርጎ የሚቆጠረው የጊፋታ በዓል በመላው የወላይታ ህዝብ ዘንድ በድምቀት እየተከበረ እንደሆነ የዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.