Fana: At a Speed of Life!

በከተማችን ባሉ የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖቻችን አገልግሎት እያገኙ ነው – ከንቲባ አዳነች

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉ 20 የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖች አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 20ኛውን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከልን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡

ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷ የምገባ ማዕከሉ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቀጨኔ መድሃኒያለም በሚባለው አካባቢ መገንባቱን ገልጸዋል።

ማዕከሉ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው አቅመደካማ ነዋሪዎች በቀን አንድ ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ የሚያቀርብ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የምገባ ማዕከሉን በ47 ሚሊየን ብር ለገነባው ቶኩማ ስታር ቢዝነስ ግሩፕ እንዲሁም ተገልጋዮቹን በቋሚነት ለመመገብ ማዕከሉን ለተረከበው የብዙአየሁ ታደለ ፋውንዴሽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ አጠቃላይ በከተማዋ ባሉ 20 የምገባ ማዕከላት ከ35 ሺህ በላይ ወገኖች አገልግሎት እያገኙ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.