Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላ የተላለፉ ከ2 ሺህ 800 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ2 ሺህ 800 በላይ ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ባለማድረግ እንዲሁም አካላዊ ርቀትን ባለማክበር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስከበር ሰው በሚበዛባቸው አካባቢዎች፣ በገበያ ስፍራዎች፣ በትራንስፖርት መስጫ ቦታዎች እና ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ስፍራዎች ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ትናንት በአቃቂ ቃሊቲ፣ በልደታ፣ በቦሌ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ህዝብ በሚበዛባቸውና በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጉንም ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የወጣውን ክልከላ የጣሱ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ነው ያስታወቀው።

በዚህም 1 ሺህ 941 ሰዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ባለማድረግ፣ 860 ሰዎች አካላዊ ርቀትን ባለመጠበቅ እንዲሁም እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የተገኙ 12 ግለሰቦች በአጠቃላይ ከ2 ሺህ 800 በላይ ግለሰቦች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላውን በመተላለፍ በቁጥጥር ስር ውለዋል ነው ያለው።

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.