Fana: At a Speed of Life!

የኢሬቻ ሳምንት የመክፈቻ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)  የኢሬቻ ሳምንት የመክፈቻ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

በመርሐ-ግብሩ በአሉን የሚያስተዋውቁ የግጥም ፣ የፋሽን ሾው ፕሮግራሞችን ጨምሮ ባህላዊ ጭፈራዎችም ቀርበዋል።

መርሐ-ግብሩ የኢሬቻን እሴቶች ለማስተዋወቅ ያለመ ሲሆን÷ በአሉ በአንድነትና በወንድማማችነት እንደሚከበር ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ  ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በብዝሃ ማንነት የደመቀች በብዙ ባህላዊ እሴቶች የተሸመነች ውብ ሀገር ናት።

ባህል የአንድ ማህበረሰብ ማንነት መገለጫ መሆኑን ገልጸው÷ በከተማዋ የሚከበሩ በአላት የመዲናዋ ድምቀቶች እና ጸጋዎች መሆናቸውን አንስተዋል።

የኢሬቻ በአል ፍቅር ከፍ የሚልበት ግለኝነት ቦታ የሚያጣበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊዋ÷ የገዳ ስርዓት አካል የሆነው ይህ በአል የሰላም እና የአንድነት በአል መሆኑን ተናግረዋል።

የአደባባይ በአላት ለቱሪዝም ዘርፍ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ ማንሳታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.