Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በወቅታዊ ሁኔታ ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች “የሕግ የበላይነት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ” በሚል መሪ መልዕክት እየተወያዩ ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች የተገኙበት የውይይት መድረክ ዋና ዓላማ በክልሉ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ተፈትቶ ሕዝቡ የሰላም ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል ነው ተብሏል።

በመድረኩ በክልሉ የተሟላ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሲከናወኑ የቆዩ ሥራዎች ተገምግመው የቀጣይ አቅጣጫዎችም ይቀመጣሉ መባሉን አሚኮ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.