Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ መርሐ -ግብር ይፋ አደረገ

 

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊየን ዩሮ ዓመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሐ-ግብር ይፋ አድርጓል።

የድጋፍ ማዕቀፉን የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተፈራርመውታል፡፡

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኮሚሽነር ጁታ በዚሁ ወቅት ድጋፉ በኢትዮጵያ ከተደረሰው የሰላም ስምምነት ማግስት ይፋ መደረጉ የአውሮፖ ህብረት ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ያሳየበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ በዋናነት በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ውስጥ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

አቶ አህመድ ሽዴ በበኩላቸው÷ ድጋፉ ለሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና ለዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ትግበራ የሚውል ይሆናል ብለዋል።

በተጨማሪም ድጋፉ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ፣ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ታዳሽ ኃይል ልማት፣ ለሰው ኃይል ልማት ግንባታ እንደሚውል አንስተዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.