Fana: At a Speed of Life!

የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ200 አካል ጉዳተኞች የምግብ አቅርቦት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ200 አካል ጉዳተኞች የተለያዩ የምግብ አቅርቦቶችን ድጋፍ አደረገ።

መምሪያው የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን የከተማዋን ነዋሪዎች በማስተባበር ከ168 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ነው ድጋፉን ያደረገው።

የመምሪው ኮሙዩኒኬሽን ሀላፊ ኢንስፔክተር ታምራት አበበ ለፋና ባደረሱት መረጃ የከተማዋ ፖሊስ መምሪያ አባላት ከደመወዛቸው 10 በመቶ በመቀነስ የተለያዩ ድጋፎችን አድርገዋል።

በተያያዘ ዜና በሻሽመኔ ከተማ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተላለፉ 20 ግለሰቦች ከ1 ሺህ 500 እስከ 9 ሺህ ብር ገንዘብ ተቀጥተዋል።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.