Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 23 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴንግ አሎር ኩዎል ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም በቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም በሱዳን ቀውስ ዙሪያ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴንግ አሎር ከፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ከሱዳን ቀውስ ጋር ተያይዞ በኢቢዬ ግዛት ጉዳይ እና የአፍሪካ ህብረት ባለው ሚና ዙሪያ የላኩትን መልዕክትም በዚህ ወቅት አድርሰዋል።

አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግስት ከሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የሚጫወተውን ሚዛናዊ እና ገንቢ ሚና እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ከአቢዬ ግዛት ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ ጉዳዩ ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲያዝና በቀጠናው የምትጫወተውን ገንቢ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥልም ነው የተናገሩት።

የአቢዬ ጉዳይም በአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት መያዝ እንዳለበትና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትን የውሳኔ ሃሳብ እንደምታከብር አስረድተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.